[ በዓሉ ግርማ]
______
ከጎራው ዘልቄ እስቲ ልነጋገር
ካለ ሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል ሀገር?
የኔ ውብ ከተማ -
ሕንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር፤
የኔ ውብ ከተማ-
መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር፤
የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር
የሰው ልጅ ልብ ነው
የሌለው ድንበር።
ህንፃው ምን ቢረዝም፣ምን ቢፀዳ ቤቱ
መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ
ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድን ነው ውበቱ?
በዓሉ ግርማ(ኦሮማይ)
______
ከጎራው ዘልቄ እስቲ ልነጋገር
ካለ ሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል ሀገር?
የኔ ውብ ከተማ -
ሕንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር፤
የኔ ውብ ከተማ-
መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር፤
የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር
የሰው ልጅ ልብ ነው
የሌለው ድንበር።
ህንፃው ምን ቢረዝም፣ምን ቢፀዳ ቤቱ
መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ
ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድን ነው ውበቱ?
በዓሉ ግርማ(ኦሮማይ)