Thursday, January 10, 2019

 ቴዲ አፍሮ ስለ አፍሪካ!
┈┈┈┈•••┈┈┈┈┈
.
#ኮርኩማ_አፍሪካ:
.
እንባም አይወጣ ከአፍሪካ ዓይኖች ስር
ሲያቅ ልጇን ባትጥለው ኮርክማ ባህር
ይዞ የመጣን አዲስ ሃሳብ፤
አለቀ ሰዋ ቤቷን ለቆ ሄዶ ሄዶ ሄዶ
ይዞ የመጣን አዲስ ሃሳብ፤
አለቀ የሳር ቤቷ ነዶ ግዶ ግዶ።
.
በስጋት ኮፈን ተይዞ እስራት
አዋቂው ሸሽቶ ራብ ነግሶ እርዛት
በምድሯ ሊቆይ ማንስ ይደፍራል
ታንኳ ላይ ወጥቶ ወንዝ ይሻገራል።
.
ውሃ ቢገባ በአፍሪካ መርከብ
አቤት ቢል ተጓዥ ሃሳብ ለማቅረብ
ይሰምጣል እንጂ ከባህር አብሮ
ቀዛፊው ላሳብ አይሰጥም ጆሮ
አለቀ ሰዋ ባህር ገብቶ ሄዶ ሄዶ ሄዶ
ኮርኩማ አፍሪካ....
.
ኮርኩማ ወንዝ አሻገረችው
ያንን የሰው ጫካ ባዶ አደረገችው
ተጉዞ ተጉዞ ሳይመጣ ቅርስ ይዞ
ኮርኩማ ባህር ጨመረችው
ለዛ ሃሩር እሳት ቆርጣ ማገደችው
ኮርኩማ አፍሪካ......
ስቃይ አይ ስቃይ
ከእንግዲ ይብቃ በምድርሽ ላይ
ሄዶ ለባዳ መሆን ሲሳይ።
===============
#ኦ_አፍሪካ!

ኦና አድርጌው ታሪኬን
የማንነት የእምነቴን ማህተብ
ለካ አፍሪካውነቴን ስቼዋለው፤
ውዬ አድሬ ስጀምር ማሰብ
ብርድ አይሞቅም፣ በጋ አይበርድም
ማንነትም ያው ነው፣ አይለወጥም
……ዜግነቴን ሳሰላስለው
.
ወና አድርጌው ሂወቴን
ዜግነቴን ሳፈላልገው
የማንነት የምነት ማተቤን
ጥበብ ርቄ ስቀዳ
ዜግነቴን ሳሰላስለው
እንዴት ልሁን ለወንዜ ባዳ
ዜግነቴን ሳፈላልገው
ጠምቶኝ ጠጣሁ ካ'ባይ ዙሪያ
ከሠው መጀመሪያ...!

No comments:

Post a Comment