Wednesday, January 9, 2019

ሁሉም መፅሀፍ አንባቢ የራሱ የሆነ ልምድ ይኖረዋል ብዬ እገምታለው የራሴን ልምድ ላካፍላችው ወደድሁ
አንድን መፅሀፍ አንብቤ ስጨርስ ስለመፅሀፉ የተወሰነ ማስታወሻ በደብተሬ እወስዳለው ሌላ የማደርገው ደግሞ የማነባቸውን መፅሀፍ የአገር ውስጥ ለብቻ ደራሲውን የመፅሀፉን አርዕስት በተራ ቁጥር እፅፋለው የውጪውንም እንደዛው አሁን ከመፅሀፍ ገጾች በጥቂቱ ምን አሉ የሚለውን እንደሚከተለው ጻፍኩላችሁ
ትንንሽ ጋኖች ትልልቅ ጆሮዎች አላቸው -- ሳቤላ
መምት ምንም አይደለም አለመኖር ግን ያስፈራል -- ምንዱባን
የሰው ልጅ ንፁህ ሀብቱ ህሊናው ነው -- ረቂቅ አሻራ
ከወጣት ብልጣ ብልጥ ይልቅ የሽማግሌ ሞኝ ብልህ ነው -- ሕያው ፍቅር
ጤናማ ህብረተሰብ የጤናማ ግለሰቦች ውጤት ነው -- ሰመመን
አስተውሎ ለሚያይ ይህቺ አለም ችግር ያለባት ቦታ ናት እኔም አስቸጋሪነቷን አውቄ በእናቴ ሆድ እንዳለሁ አልወለድም ብዬ ነበር ግን ተወልደናልና ከዚች አለም እስክንገላገል ድረስ በትዕግስትና በቆራጥነት ለእውነተኛው ነገር መታገል አለብን -- አልወለድም
ከውጪ የሚመጣ ምንም ነገር የለም ሁሉም ከውስጥ ነው የሚመጣው -- ሚስጥሩ
ስጥ ይሰጥሃል በሰፈርክበት መስፈሪያ ትሰፈርበታለህ -- መፅሀፍ ቅዱስ
አበቃሁ መልካም የንባብ ክረምት ለሁላችን ይሁን
@BookforEthiopia
bookforethiopia.blogspot.com

No comments:

Post a Comment